ማህደር ቤተ-መጽሓፍት
ግባምዝገባ

ሕጋዊ ሰነዶች

  • የመረጃ ኣያያዝ ስርዓት
  • የኣገልግሎት ፓሊሲ
  • የቅጂ መብት ፖሊሲ
  • የተመላሽ ገንዝበ ፓሊሲ
  • የደራሲ ስራ ፓሊሲ

የደራሲ ስራ ፖሊሲ

የታደሰበት ቀን፦ ሰኔ 12, 2018 ዓ.ም

ይህ ፓሊሲ ለሁሉም ጸሓፊዎችና ደራሲዎች የሚመለከት ሆኖ ጽሑፋቸውን ወደ ማህደር ቤተ-መጽሓፍት በመጫን በዚህ ፓሊሲ እንደሚገዙ የሚስማሙ ይሆናል። ይህ ፖሊሲ የአገልግሎት ውሎቻችንን እና የቅጂ መብት ፖሊሲያችንን ያሟላል።

1. የጽሑፍ የጥራት ደረጃ

  • ዋና ሥራ፦ የመጽሓፉ ይዘት የእርስዎ ፈጠራ ሊሆን ይገባል። የሌላ ሰውን ስራ እንደራስ ኣድርጎ ማቅረብ ፍጹም የተከለከል ነው
  • ስለመጽሓፍ መረጃ፦ ርዕስ፣ የደራሲ ስም፣ ቋንቋ እና ሌሎች መረጃዎች የመጽሓፉን ትክክለኛ ይዘት ሊወክሉ ይገባል
  • ቋንቋ እና ጥራት፦ መጽሓፉ በነዚህ ቋንቋዎች ሊጻፍ ይገባል ትግርኛ፣ ኣማርኛ፣ እንግሊዝኛ ወይም ኦሮምኛ። መጽሓፉ በትክክል የተጻፈ እና በትክክል የተጠናቀቀ መሆን ይገባል
  • ሽፋን ምስል፦ በመጽሓፉ ሽፋን የራቆት ምስል ማሳየት፣ ወይም ሌላ ኣጸየፊ ምስል ማሳየት የተከለከለ ነው

2. የተከለከሉ ይዘቶች

  • የሌሎች ሰዎችን የቅጂ መብት የሚጣረስ ከሆነ
  • ስም-ማጥፋት ወይም ሐሜት የሚፈጥሩ ይዘቶቹ
  • ዘር፣ ብሔር፣ ሃይማኖት፣ ጾታ ወዘተ መሰረት ያደረገ ጥቃት የሚያደርስ ከሆነ
  • ህፃናት ለጾታዊ ጥቃት እንዲጋለጡ ጥሪ የሚያቀርብ ወይም የሚያስተጋባ ከሆነ
  • ጥቃት፣ ሽብርተኝነት ወይም ህጋዊ ያልሆኑ ድርጊቶቹ የሚያሞካሹ ይዘቶች
  • በኣጠቃላይ ማንኛውንም የኢትዮጵያ ሕጎቹ የሚጥሱ ይዘቶች

3. ሊኖርዎ የሚገቡ ፈቃዶች

መጽሓፍ ከመጫንዎ በፊት የሚከተሉትን ፈቃዶች መያዝዎን ያረጋግጡ፦፦

  • በመጽሓፉ የተካተተውን ይዘት የመባዛት፣ ለሌሎች የማዳረስ፣ ለገበያ የማቅረብ መብት ፈቃድ
  • ከሚመለከተው ሶስተኛ ኣካል መጽሓፉን የመሸጥ፣ ለሌሎች የማዳረስ ፈቃድ
  • ለማህደር ቤተ-መጽሓፍት በ ክፍል 4 ላይ የተዘረዘሩትን መብቶች የመስጠት ፈቃድ

4. ለማህደር ቤተ-መጽሓፍት የሚሰጧቸው መብቶች

ይዘቱ ሲጭኑ ለማህደር ቤተ-መጽሓፍት ያልሆን-ሚስጥር ዓለምአቀፍ ፈቃዱ ሊሰጧቸው፦

  • መጽሓፉ በፕላትፎርሙ ላይ ለተጠቃሚዎች የማቅረብ፣ የማስቀመጥ፣ ለተሻለ ኣቀራረብ ሲባል የመጽሓፉን ቅርጽ የመለወጥ።
  • የመጽሓፉን ሽፋን ምስል፣ ርዕስ፣ የደራሲ ስም፣ የመጽሓፉን ይዘት በከፊል ወይም በሙሉ የመሳሰሉትን ዝርዝር ይዘቶች ለተጠቃሚዎች የማሳየት
  • መጽሓፉን በተለያዩ የስክሪን መጠኖች ለማሳየት የመጽሓፉን ቅርጽ የመለወጥ

ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ጻሓፊዎች ሙሉ የባለቤትነት መብት ይይዛሉ። ይህ ፈቃድ የመጽሓፉን ባለቤትነት ወደ ማህደር ቤተ-መጽሓፍት አያስተላልፍም።

5. የመጽሓፉን ይዘት የመመርመር ሂደት

ሁሉም ሥራዎች ከሕትመት በፊት ሪቪው ይደረጋሉ። የሪቪው ሂደት እስከ 5 ቀናት ሊፈጅ ይችላል። መጽሓፉ የሚጠበቀውን የጥራት ደረጃ የማያሟላ ከሆነ ውድቅ ሊደረግ ይችላል ወይም ማሻሸያ እንዲቀርብ ይጠየቃል።

6. መጽሓፉን ከፕላትፎርሙ የማውረድ፣ ጸሓፊውን የማገድና መሰል ቅጣቶች

የመጽሓፉ ይዘት የማህደር ዲጂታል ቤተ-መጽሓፍት ፓሊሲ የሚጥስ ሆኖ ሲገኝ፣ ያለምንም ማስጠንቀቅያ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ሊወሰዱ ይችላሉ፦

  • መጽሓፉን ማውረድ ወይም እንዳይነበብ መከልከል
  • ኣካውንትዎን ማገድ ወይም ማስወገድ
  • በማጭበርበር የተፈጸመውን ክፍያ ማስመለስ
  • ህጋዊ ኣካሄድ የተላለፈውን ሰው ለሚመለከተው ሕጋዊ ኣካል ኣሳልፎ መስጠት

ውሳኔ ለመቃወም ወደ contact@mahderbooks.com በ 14 ቀናት ውስጥ ይፃፉ።

7. የገቢ ድርሻ እና ክፍያ ሁኔታ

ደራሲዎች ከጠቅላላ ሽያጭ 85% ይቀበላሉ — ይህ የሚሆነው የክፍያ ስርዓት ለመፈጸም የሚያስፈልግ ወጪ ከተሸፈነ በጓላ ነው። ክፍያው ለጸሓፊው በየወሩ የሚደርስ ይሆናል። ይሁን እንጂ ከመጽሓፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን የገንዘብ መጠን ደራሲው ከተስማማበት ያነሰ የክፍያ ገደብ (minimum payout threshold) በላይ መሆን ኣለበት። የተመላሽ ገንዘብ ክፍያ ፓሊሲ በ የተምላሽ ገንዘብ ክፍያ ፖሊሲ እንደተዘረዘረው የተለየ ሊሆን ይችላል።

8. የፖሊሲ ለውጦች

ፕላትፎርሙ ሲያድግ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ሊያደርግ ይችላል። የፓሊሲ ለውጦች በተግባር ከመዋላቸው በፊት፣ 14 ቀናቶች ኣስቀድሞ በዌብሳይቱ ይስተዋወቃል።

9. አድራሻ

ስለ ፖሊሲ ጥያቄ ለመጠየቅ በ contact@mahderbooks.com ይጻፉ።

ፈልግ

  • መጽሓፍት
  • ትግርኛ
  • አማርኛ
  • እንግሊዝኛ

ጸሓፊዎች

  • የደራሲ ቦታ
  • እንደ ደራሲ ተመዝገብ
  • መጽሓፍ ጫን

ድርጅት

  • ስለ እኛ
  • ፈልጉን

ሕጋዊ ሰነዶች

  • የመረጃ ኣያያዝ ስርዓት
  • የኣገልግሎት ፓሊሲ
  • የቅጂ መብት ፖሊሲ
  • የተመላሽ ገንዝበ ፓሊሲ
  • የደራሲ ስራ ፓሊሲ

© 2026 ማህደር ዲጂታል ቤተ-መጽሓፍት። የደራሲ መብት የተጠበቀ ነው።